የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሃገሪቱን የገቢ ንግድ ለማሳለጥ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ለደንበኞቹ እያቀረበ የሚገኝ ባንክ መሆኑን አስታዉቋል።
ባንኩ በዛሬው እለት (ማለትም እ.ኤ.አ 04/04/2025) የደምበኞቻችንን የውጪ ምንዛሪ ጥያቄ ለመመለስ እ.ኤ.አ እስከ 31/03/2025 ድረስ ባጠቃላይ በቁጥር 711 ደንበኞች ያቀረቡትን ጥያቄዎች በሙሉ በመገምገም ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ ብዛታቸው 698(98%) ለሆኑ ደንበኞች በድምሩ የ122.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድልድል ማድረጉን ገልጿል።
የቀሩት ጥቂት ደምበኞች ጥያቄ ተጨማሪ የመረጃ ማጥራት ስራ ተሰርቶ በቅርቡ የሚታይላቸው ይሆናል ሲል አስታዉቋል።
በቀጣይም ባንኩ ለደንበኞቹ የውጪ ምንዛሪ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን መግለጹን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ የትስስር ገጽ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።