AMN-የካቲት 23/ 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ ምርትና አገልግሎቶቹን ለዕይታ አቅርቧል።
በዐውደ ርዕዩ ላይ የሮቦቲክስ እና የሆሎግራም ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ የበለፀጉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ መተግበሪያዎች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
ዐውደ ርዕዩ ለተከታታይ 10 ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት ተመርቆ መከፈቱ ይታወሳል።