AMN-የካቲት 29/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በ2025 የኢትዮጵያ ኤክስፖ ለሚሳተፉ አካላት ፕሮፖዛል እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርቧል።
በፈረንጆቹ ከግንቦት ከ16 እስከ 18 ቀን 2025 በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው በዚህ ኤክስፖ ላይ ተመራማሪዎች፣ ምሁራን እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ፕሮፖዛላቸውን እንዲያቀርቡ ጋብዟል።

በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ዘመን የሳይበር ደህንነት፣ የሳይበር ደህንነት በዘመናዊ ከተሞች፣ በኳንተም ስሌት፣ ፋይንቴክ ዙሪያ ፕሮፖዛላቸውን እንዲያቀርቡ ነው ጥሪ ያቀረበው።
የፕሮፖዛል ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን በፈረንጆቹ ሚያዝያ 20 እንዲሁም የውጤት ማሳወቂያ ጊዜ ሚያዝያ 30 ቀን 2025 መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።