AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም
5ኛው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ አትሌት የማነ ፀጋይን ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።
5ኛው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስአበባ በመካሄድ ላይ ሲሆን፤ ማህበሩ በጉባኤው ላይ ከ2014 እስከ 2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም እና የፋይናንስ ሪፖርት እንደሚያቀርብ መመላከቱ ይታወቃል፡፡
ማህበሩ በተጨማሪም አዳዲስ ስራ አስፈጻሚ አባላትን የሚመርጥ ሲሆን፤ በሂደቱም አትሌት የማነ ፀጋይን ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።