የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

AMN- መስከረም 9/2017

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።

ሽልማቱ የተበረከተው ኮርፖሬሽኑ 35ኛ ዓመቱን ባከበረበት ደማቅ መርሐ ግብር ላይ ሲሆን አየር መንገዱ ላበረከተው የላቀ አገልግሎት እና የላቀ የስራ አጋርነት ዕውቅና የተሰጠበት ነው።

ይህ ሽልማት ለዛምቢያ ኤርፖርት ዕድገት በመንገደኛ እና በዕቃ ጭነት የአገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ማሳያ መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review