የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን አዲስ በረራ ጀመረ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን አዲስ በረራ ጀመረ

AMN- ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን አዲስ በረራ ጀመረ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ የሱዳን የወደብ ከተማ ወደሆነችው ፖርት ሱዳን በየቀኑ የሚደረግ አዲስ በረራ ጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ_ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፤ የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ሃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ በኢትዮጵያ የሱዳን ኤምባሲ ምክትል የሚሲዮን መሪ ሱአድ አሊና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን በየጊዜው እያሰፋ መሆኑን በማንሳት በተለይ የአፍሪካ ከተሞችን በአየር ትራንስፖርት በስፋት እያስተሳሰረ ይገኛል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ 61 ከተሞች ላይ የሚበር ሲሆን ዛሬ ወደ ፖርት ሱዳን የተጀመረው በረራ አየር መንገዱ በአፍሪካ ከተሞች ያለውን መዳረሻ ወደ 62 የሚያደርሰው እንደሚሆን ገልጸዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም አየር መንገዱ ፖርት ሱዳንን አዲስ መዳረሻ ለማድረግ በእቅዱ ከያዛቸው መካከል መሆኑን አስታውሰዋል።

የበረራው መጀመር የሁለቱን አገራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግንኙነት ንግድና ቱሪዝምን ይበልጥ እንደሚያሳልጥ ገልጸዋል።

የፖርት ሱዳን አዲስ በረራም አየር መንገዱ ያሉትን ዓለም አቀፍ መዳረሻ ወደ 140 ከፍ እንደሚያደርገው ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review