የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” ሽልማት አሸነፈ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” ሽልማት አሸነፈ

AMN-የካቲት 14/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የ2025 የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት ልሕቀት ሽልማት መርሀግብር “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” በመባል ዕውቅና መቀዳጀቱን አየር መንገዱ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት ኤርፖርት” እና “ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ ያለ የዓመቱ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” በመባል ተደራራቢ ዕውቅና እና ሽልማት ተችሮታል።

እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ላለው ዘርፈ ብዙ ዓለም አቀፍ አገልግሎት አስተማማኝነትና ቅልጥፍና ማረጋገጫዎች መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review