የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎንደር አየር ማረፊያን ሙሉ ግንባታ ለማከናወን ቃል ገባ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎንደር አየር ማረፊያን ሙሉ ግንባታ ለማከናወን ቃል ገባ
  • Post category:ልማት

AMN- ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ1ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የጎንደር አየር ማረፊያን ሙሉ ግንባታ ለማከናወን ቃል ገባ፡፡

ኑ ጎንደርን እንሞሽር ታላቅ የገቢ ማሠባሠቢያ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 1ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በመበጀት የጎንደር አየር ማረፊያን ሙሉ ግንባታ አከናውናለሁ ሲል ቃል መግባቱን አሚኮ ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪም አየር መንገዱ የአምስት ኪሎሜትር የመንግድ ሥራ እደሚያከናውንም ገልጿል።

የጎንደር ኮሪደር ልማት ሁለተኛ ዙር ግንባታ “ኑ ጎንደርን እንሞሽር” የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር አሁንም ቀጥሏል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review