የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 17 ነጥብ 1 ሚሊየን መንገደኞችን በማጓጓዝ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

AMN- ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 17 ነጥብ 1 ሚሊየን መንገደኞችን በማጓጓዝ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱን ዓመታዊ አፈፃፀም በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አየር መንገዱ በዓመቱ 5 ዓለም አቀፍ አዳዲስ መዳረሻዎችን ስለመጀመሩ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህም የአየር መንገዱን ዓለም አቀፍ መዳረሻ 139 አድርሶታል ብለዋል።

በዓመቱ ወደ 3 የሃገር ውስጥ ከተሞች በረራ የጀመረው አየር መንገዱ የሃገር ውስጥ መዳረሻዎቹ አዲስ አበባን ሳይጨምር 21 መድረሳቸውን አቶ መስፍን ተናግረዋል።

በአንድ ዓመት ውስጥ 17 ነጥብ 1 ሚሊየን መንገደኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ መጓጓዛቸውንም ዋና ስራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በዓመቱ 7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ወይም 4002 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱ የተጠቆመ ሲሆን 5 ቢሊዮን ቢሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘው ከመንገደኞች ብቻ ነውም ተብሏል።

ከዓለማችን ግዙፍ አየር መንገዶች ውስጥ አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አምስት አህጉራት በመብረር በ139 መዳረሻዎች ላይ ያርፋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review