የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል ተገቢ እና ጠቃሚ ሪፎርሞችን በትጋት በመፈፀም ውጤታማ ማድረግ የመንግስት ትኩረት ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል ተገቢ እና ጠቃሚ ሪፎርሞችን በትጋት በመፈፀም ውጤታማ ማድረግ የመንግስት ትኩረት ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል ተገቢ እና ጠቃሚ ሪፎርሞችን በትጋት በመፈፀም ውጤታማ መሆን የመንግስት ትኩረት በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደንበኛ አገልግሎት መስጫ እና በጥሪ ማዕከል የመስክ ምልከታ አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ እያከወናቸው የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎችን ተመልክተናልም ብለዋል፡፡

አገልግሎቱ በርካታ ደንበኞችን የማስተናገድ ዐቅሙን በማሳደግ እንግልትን ለመቀነስና ግልጽ የአሠራር ሥርዓትን ለመተግበር ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ተወያይተናል ሲሉም አመልክተዋል፡፡

በደንበኛ አገልግሎት መስጫ፣ በዳታ ሴንተር እና በጥሪ ማዕከል እየተተገበሩ በሚገኙ ሥራዎች፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን በማቅረብ ተልዕኮ ሂደት የሚያጋጥሙ መሠረታዊ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችሉ ተግባራት ላይም አቅጣጫ አስቀምጠናል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review