AMN – ጥር 24/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ወደ ሃላፊነት የመጣው መጅሊሱ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል።
እነዚህን ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል ከጥቂት ወራት በኋላ ለቀጣይ 5 ዓመታት ተቋሙን የሚመሩ የአዳዲስ አመራሮች ምርጫ በመላ ሀገሪቱ ይካሄዳል ብለዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በዛሬ ጉባዔው የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፣ በዚህም የተዘጋጀ የምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያና ማስፈጸሚያ ሰነድን አጽድቋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ዕድሜው ለምርጫ የደረሰ ሁሉም ሕዝበ ሙስሊም በአካባቢው በሚገኝ መስጂድ በመመዝገብ በምርጫው በንቃት እንዲሳተፍም ጥሪ
ቀርቧል።
ምርጫውን ለማከናወን የሚያስችል በጀት መጽደቁ የተጠቆመ ሲሆን፣ ሕዝበ ሙስሊሙ ምርጫውን ሽፋን በማድረግ አንድነቱን አደጋ ላይ ከሚጥሉ እንቅስቃሴዎች እራሱን እንዲጠብቅም መልዕክት ተላልፏል፡፡
በተጨማሪም በጉባዔው የፌዴራል የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት ምርጫ የተካሄደ ሲሆን፣ አባላቱም ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
በመሀመድኑር አሊ