AMN – ጥር 16/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የፖሊስ ተቋማት ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡
ኮሚሽነር ጀነራሉ በVIP እና በሁነቶች ደኅንነት ጥበቃ፣ በአድማ መከላከል እና በሳይበር ወንጀል ምርመራ ዙሪያ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በዙር ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኦፊሰሮች ስልጠና ሲሰጡ ለቆዩት ለተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለዱባይ ፖሊስ አሰልጣኞች የዕውቅና ሠርተፊኬት ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ለተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የዱባይ ፖሊስ ለሰጡት ስልጠና፣ ላደረጉት የማቴሪያል ድጋፍ እና ሰማርት ፖሊስ ጣቢያ ለማቋቋም እየሠሩ ላሉት ሥራ በራሳቸውና በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሠራዊት ሥም ምስጋና ማቅረባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።