የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክለቦች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባው ተጠቆመ

You are currently viewing የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክለቦች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባው ተጠቆመ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አመራሮችና ስራ አስፈፃሚ አባላት ጋር በእግር ኳሱ ዕድገት ተግዳሮቶችና በፌዴሬሽኑ አሰራር ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በተከናወነው የመስክ ምልከታ ወቅት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ እንዳሉት በእግር ኳሱ ውጤት ለማምጣት ፌዴሬሽኑ በክለቦች ውጤታማነት ላይ አተኩሮ ሊሰራ ይገባል ።

ቋሚ ኮሚቴው ለእግር ኳሱ ውጤት መሻሻል ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በበኩላቸው ፌዴሬሽኑ የሀገሪቱን እግር ኳስ ውጤት ለማሻሻል በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል

የበጀት እጥረት፣ የክለቦች ተተኪ ለማፍራት አቅደው አለመስራት፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ከውጭ ሀገራት አምጥቶ ለማጫወት ያሉ የህግ ክፍተቶች፣ ከተለያዩ አካላት ለእግር ኳሱ የሚሰጡ ትኩረቶች ማነስ እና ደረጃውን የጠበቀ እስቴዲየም ያለመኖር የኳሱን እድገትና ውጤት እንደጎዳው ተናግረዋል።

በዘርፉ ያለውን ችግር ለመፍታት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ፌደሬሽኑ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸውም ማሳሰባቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr

Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9

Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8

Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review