AMN- መስከረም 7/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ማስረጃን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ መቅረፅና ውሳኔ መስጠት የሚያስችል የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ይፋ ሆኗል።
የዓለም የቱሪዝም ቀንን በማስመልከት ከኢጋድ እና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የቱሪዝም ሳተላይት አካውንቱን ይፋ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ማስረጃን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ ለመቅረፅና ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቱሪዝም እና የስታስቲክስ ክፍሎች፤ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና አጋር ተቋማት ጋር በትብብር የተዘጋጀው ይሄው የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በላይ ጊዜ ወስዷል ተብሏል።
የሳተላይት አካውንቱ መረጃዎችን በመሰነድ በማስቀመጥ ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ አቅም በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስችል መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡