የክልሎችን እና የሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችን የዳያስፖራ ማኀበራት በመያዝ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኀበራት ሕብረት ለመጀመሪያ ጊዜ ተመስርቷል፡፡
ኅብረቱ ትናንት መመሥረቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት፣ ህብረቱ የመመሥረቻ እና የመተዳደሪያ ደንቡን በማጽደቅ፣ ቦርድ፣ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ዋና ፀሐፊ በመምረጥ ስብሰባውን አጠናቋል ብለዋል።
ህብረቱ በዳያስፖራው ቁልፍ ጉዳዮች ላይ እንደሚሰራ ተስፋ እንደተጣለበት አምባሳደር ፍጹም መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡