የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ SWAT ቡድን በዓለም አቀፍ የ2025 የSWAT ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ዱባይ አቀና

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ SWAT ቡድን በዓለም አቀፍ የ2025 የSWAT ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ዱባይ አቀና

AMN – ጥር- 18/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን (SWAT) የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ባዘጋጀቺው ዓለም አቀፍ የ2025 የSWAT Challenge ላይ ለመወዳደር ወደ ዱባይ አቅንቷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ SWAT ቡድን በቂ ዝግጅት አድርጎ ዱባይ በአል ሩዋይ ከተማ እ.ኤ.አ. የካቲት 1 ቀን 2025 በሚጀምረው የSWAT Challenge ውድድር ላይ፤

በታክቲካል ኦፕሬሽን ቻሌንጅ ፣ በጥቃት ቻሌንጅ ፣ በVIP አመራር የማዳን ተልዕኮ ፣ በከፍተኛ ታወር መውጣትና መውረድ ፣ በመሰናክል ኮርስ እንደሚወዳደር ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ቡድኑን በሸኙበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ቡድኑ ተወዳድሮ ከማሸነፍ ባለፈ በፈጣን ምላሽ ሰጭነት ላይ ተሞክሮውን ለማካፈል፣ ከዓለምአቀፍ ልምምዶች ጋር ለመተዋወቅ፣ ከተለያዩ ሀገራት ጥሩ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም እና ዝግጁነቱን የበለጠ ለማሳደግ ውድድሩ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል።

በውድድሩም አሜሪካና ቻይናን ጨምሮ ከ50 ሀገራት የተውጣጡ ከ120 በላይ የSWAT ቡድን እንደሚሳተፉ የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review