የኢትዮ-ሳውዲ አረቢያ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በሪያድ መካሄድ ጀምሯል።
በፎረሙ ከሁለቱም ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የቢዝነስ መሪዎችና የንግዱ ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።
በተያያዘም የኢትዮ-ሳዑዲ አረቢያ የጋራ ንግድ ምክር ቤት ስብሰባ በሪያድ ተካሂዷል።
ስብሰባውን በኢትዮጵያ ወገን የንግድ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር ሃሰን አብዱላሂ(ዶ/ር) እና በሳዑዲ ወገን የጋራ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር አብድላህ አላጃሚ በጋራ መርተውታል።
በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ታሪካዊ ትብብር በኢኮኖሚው ዘርፍ ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል።
መድረኩ በሀገራቱ መካከል አዲስ የኢኮኖሚ ትብብር እና የስትራቴጂክ አጋርነት ምዕራፍ እንደሚፈጥር ተነስቷል።
በስብሰባው በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በኮንስትራክሽን ዘርፎች አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።