የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና ኤሌክትሮኒክስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ

You are currently viewing የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና ኤሌክትሮኒክስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ

AMN- መስከረም 15/2017 ዓ.ም

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና ኤሌክትሮኒክስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ University of Electronics Science and Technology of China (UESTC) ተቋርጦ የነበረውን የበትረ-ሳይንስ ስኮላርሽፕ ፕሮግራም ለማስቀጠል መክረዋል።

የጋራ ምክክሩ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የአጭርና የረጅም ግዜ ስልጠናዎችን በማመቻቸትና በጋራ በመስራት በዘርፉ በቂና ብቁ የሆነ የሰው ሀይል ለማፍራት ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ የቴክኖሎጂ አማካሪ (ዶ/ር) ስሜነው ቀስቅስ ቀደም ሲል በበትረ ሳይንስ ስኮላርሽፕ ፕሮግራም ከቻይና ኤሌክትሮኒክስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (UESTC) ከ100 በላይ በመጀመሪያ ዲግሪ ለትምህርት ተልከው ተጠቃሚ መሆናቸውንና ከተመረቁት ውስጥ 69 የሚሆኑት በዩኒቨርስቲው በቀጥታ የማስተርስ ዲግሪ ስኮላርሽፕ ተሰጥቷቸው በመማር ላይ መሆናችውን ገልፀዋል።

ከቻይና ኤሌክትሮኒክስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (UESTC) የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጓንግቹን ሉኦ ከአሁን በፊት የነበረንን ግንኙነት በማደስ ተቀራርበን ሊያሰራን የሚችል ጉዳዮችን በመለየት በጋራ ለመስራት ዝግጁ ነን ብለዋል።

በቀጣይ የተጀመሩ ትብብሮችን በማጠናከርና ተጨማሪ የትብብር ዘርፎችን በመለየት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቶ እንደሚፈራረሙና እንደሚተገብሩም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review