የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ካለን አካፍለን ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ እሴቶችን የምናዳብርበት ነው፡-አቶ ጥራቱ በየነ

You are currently viewing የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ካለን አካፍለን ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ እሴቶችን የምናዳብርበት ነው፡-አቶ ጥራቱ በየነ

AMN – ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ካለን አካፍለን ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ እሴቶችን የምናዳብርበት ነው ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በወረዳ 8 በተገነባው ሎኮስት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በዓሉን ምክንያት በማድረግ የምሳ ፕሮግራም አካሂዷል።

በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በዓሉን ካለን አካፍለን ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ እሴቶችን የምናዳብርበት ነው ብለዋል፡፡

በዓሉ የሠላም፣የደስታ፣የጤና እንዲሆን እመኛለው ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በነዋሪዎቹ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አውስተው የገና በዓበአብሮነት፣በወንድማማችነትና በእህትማማችነት በጋራ የምናከብረው በዓል ነው ማለታቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review