የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

May be an image of 1 person

AMN – ታኀሣሥ 28/2017 ዓ.ም

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

አቶ ቡልቻ ታዋቂ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ፣ መርህ ያላቸው ፖለቲከኛ፣ ለዴሞክራሲ ተሟጋች የነበሩ እና ሀገራቸውንና አፍሪካን በትጋት ያገለገሉ አንጋፋ ሰው መሆናቸውን ዋና ፀሐፊው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውሰዋል፡፡

በአገልግሎታቸው እና በእውቀታቸው ያሳረፉት አሻራ ቀጣዩን ትውልድ እንደሚያነሳሳም ገልጸዋል።

ዋና ፀሃፊው ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

All reactions:

104104

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review