የእስራኤሉ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለ200 ህፃናት ነፃ የልብ ህክምና ሊሰጥ ነው

You are currently viewing የእስራኤሉ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለ200 ህፃናት ነፃ የልብ ህክምና ሊሰጥ ነው

AMN- መስከረም 10/2017 ዓ.ም

የእስራኤሉ ሴቭ ቻይልድስ ኸርት ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለ200 ኢትዮጵያውያን ህፃናት ነፃ የልብ ህክምና ሊሰጥ ነው

የልዑካን ቡድኑ ባለፋት አራት ቀናት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይስድ ሆስፒታል እና በኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል አፋጣኝ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ህፃናት መለየቱን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ድርጅቱ ከፈረንጆቹ አቆጣጠር 1996 ዓ.ም ጀምሮ ከ900 በላይ ለሚሆኑ ህፃናት ህክምና መስጠቱን ተናግሯል።

ለልብና ተያያዥ ህመሞች ፣ለቀዶ ህክምና ባለሙያዎች፣ለተንከባካቢ ነርሶችና ለቴክኒሺያኖች ድርጅቱ ስልጠና መስጠቱም ተጠቁሟል።

በመግለጫው ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ቶመር ባር ላቪ ድርጅቱ በእስራኤል አገር ባለው የዎልፍሰን የህክምና ማዕከል በርካታ ኢትዮጵያውያን ህፃናትን እያከመ ስለመሆኑ አንስተዋል።

የእስራኤል ኤምባሲም ድርጅቱ በኢትዮጵያ በቀጣይ ለማከናወን ላቀደው ስራ ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው የጠቀሱት።

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር አንዱዓለም ደነቀ ከድርጅቱ ጋር ባለፈው ዓመት በተፈራረምነው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት በርካታ ህፃናትን ወደ እስራኤል በመላክ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ሴቭ ቻይልድስ ኸርት እ.አ.አ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ በ70 አገራት ከ7ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህፃናት ከልብ ጋር የተያያዘ ህክምና መስጠቱንም በመርሀ ግብሩ ላይ ተጠቅሷል።

በትእግስት መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review