የከተማችን ሕዝብ ያደረግነውን ጥሪ ተቀብሎ በማለዳ በነቂስ ወጥቶ በተከላው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የከተማችን ሕዝብ ያደረግነውን ጥሪ ተቀብሎ በማለዳ በነቂስ ወጥቶ በተከላው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

እንደ ሀገር በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብርን በአዲስ አበባ በ168 የመትከያ ቦታዎች በ250 ሔክታር መሬት ላይ ዛሬ ማለዳ ማስጀመራቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “የከተማችን ሕዝብ ያደረግነውን ጥሪ ተቀብሎ በማለዳ በነቂስ ወጥቶ በተከላው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ ባለሃብቶች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት አመራሮች ‘የጀመርነውን ሳንጨርስ አንገባም’ በሚል በችግኝ ተከላው ላይ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

እንደ ሀገር ለመትከል ከተያዘው በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ውስጥ ስድስት ሚሊዮኑን ችግኞች የምትተክለው አዲስ አበባ ናት ሲሉም ነው ከንቲባዋ መልእክታቸውን ያስተላለፉት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review