የከተማችን ነዋሪ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ እንዲሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል ማድረግ ያስፈልጋል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ታህሣሥ 6/2017 ዓ.ም

የከተማችን ነዋሪ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ እንዲሁም ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል ማድረግ ይገባል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

“ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለሁሉአቀፍ የማህበረሰብ ጤንነት!” በሚል መሪ ቃል የጤና ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በመሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወናቸውን ከንቲባዋ አስታውቀዋል።

ከንቲባዋ መርሐግብሩን አስመልክተው በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣” የከተማችን ነዋሪ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ እንዲሁም ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል በማድረግ ሁሉም በየአካባቢው እና በየመስሪያ ቤቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንዲያደርግ መስራት ይኖርብናል” ብለዋል።

ጎዳናዎች ጽዱ እና ለጤና ተስማሚ እንዲሆኑ ተደርገው መገንባታቸውን የገለፁት ከንቲባዋ “ሁላችንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እያደረግን እንንከባከባቸው” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review