
AMN – ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም
የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን፣ በተደራጀ የዝርፊያና የስርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር የማዋል ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ያለውን የፀጥታ ሁኔታን በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን፣ በተደራጀ የዝርፊያና የስርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር የዋሉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ ላይ ተመላክቷል።
አሁን ላይ የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ሰላምና ደህንነት በተሻለ ሁኔታ ላይ ያለ መሆኑን በውይይታቸው አንስተው በቀጣይም ይህኑን የሰላም ሁኔታ የበለጠ አጠናክረው ለማስቀጠል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ተቀምጠው የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የሚያውኩና በማንኛውም ሀኔታ ለከተማዋ ፀጥታና ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ቡድኖችን ያማከለ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ መነሳቱን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያሳያል።