የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጀምሯል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጀምሯል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ሚያዝያ 20/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ በሰፈሩት መልእክት የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

በግምገማ መድረካችን ያለፉት ዘጠኝ ወራት ስኬታማ ስራዎችን በመፈተሽ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል ዝርዝር ግምገማ የምናደርግ ሲሆን፣ ታቅደዉ ያልተፈፀሙ እና በስድስት ወራት የስራ ግምገማችን ወቅት በዝርዝር ለይተን በሰጠነው ግብረመልስ እና አቅጣጫ መሰረት የህዝብ የቅሬታ ምንጭ የሆኑ ክፍተቶች አፈታትን በጥልቀት የምንገመግም ይሆናል።

በተጨማሪ በመድረኩ የአመራራችንን ችግር የመፍታት አቅም፣ የሚመራውን ተቋም ክፍተት በመለየት ምን ያህል ማሻሻል እንደቻለ እና ክፍተቶችን አስቀድሞ ለይቶ በፍጥነት መፍታት ላይ የመጡ ለውጦች ይገመገማሉ።

የግምገማ መድረኩ በቀሪ ሶስት ወራት እቅዶቻችንን በተሟላ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችሉ መግባባቶች ላይ የምንደርስበት ሲሆን፣ የለየናቸዉን ክፍተቶችን በማረም ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ለማገልገል ራሳችንን ይበልጥ የምናዘጋጅበትም ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review