የከተማ የግብርና ልማትን በማጠናከር ወደ ግብርና መር ኢንዱስትሪ መቀየር የሚችልበትን አመላካች ውጤት ማየት ተችሏል፡- ዶ/ር ፍፁም አሰፋ

AMN – ታኅሣሥ -5/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ባሉ ቁልፍ የልማት ስራዎች ላይ እየተካሄደ ያለው የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስራ 4ኛ ቀኑን ይዟል ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒሰቴርና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የሦስተኛ ቀን የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስራ በቦሌና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የተሰሩ ቁልፍ የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ ( ዶ/ር ) ያየናቸው ስራዎች የወደፊት የእድገት ተስፋዎቻችን ስለሆኑ ሁላችንም አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ልናሰፋቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ግብርና ሁሉን የሚይዝ ህይወትን የተሻለ የሚያደርግ ነው ያሉት ሚኒስትሯ መንግስት የተቀናጀውን የከተማ የግብርና ልማትን በማጠናከር ወደ ግብርና ኢንዱስትሪ መቀየር የሚችልበትን አመላካች ውጤት ማየት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በበኩላቸው በሀገራችን ትልቅ ሚና ያለውን የግሉን ዘርፍ በመደገፍና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ለኢኮኖሚያችን እድገት ያለውን አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ስላልሰራንና አቅማችንን አሟጠን ስላልተጠቀምን እንጂ ኢትዮጵያ ሰፊ የመልማት አቅም ያላት ሀብታም ሀገር ናት ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ በምሳሌነት የሚጠቀሱትን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በማስፋት ከውጪ የምናስገባውን ከማስቀረትም አልፎ የምንልክበት እና የውጪ ምንዛሪ የምናገኝበትን ስርዓት መፍጠር አለበት ብለዋል።

ጉብኝቱ የቦሌ ክፍለ ከተማ ያሉ የጋርመንት ምርቶችን፣ በቡና ላይ እየተጨመሩ ያሉ እሴቶችን፣ በፈርኒቸር ስራ ላይ የተሰሩ ውጤቶችን፣ በትምህርት ቤት የተደረጉ ማስፋፊያዎች፣ የወጣቶች የስፖርት ማዕከሎችን፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርናንና የሌማት ቱርፋቶችን የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስኬታማ በሆነ መልኩ አጠናቋል፡፡

በመጨረሻም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመወያየት ስራዎችን ዲጂታል ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችን በተቋሙ በመገኘት መጎብኘታቸውን ከኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review