የከተማ ግብርና በኢትዮዽያ ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት

You are currently viewing የከተማ ግብርና በኢትዮዽያ ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት

AMN- ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም

የከተማ ግብርና በኢትዮዽያ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ ፡፡

እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች በግቢዎች ውስጥ በጥቅም ላይ ያልዋሉ ስፍራዎችን የምግብ ዋስትናን ወደ ሚያሳድጉ፣ ዘላቂነትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ወደ ሚያመጡ አረንጓዴ ስፍራነት እየተቀየሩ መሆኑንም ገልፃል።

አነስተኛም ሆነ ትላልቅ ኮንቴይነሮችን፣ እንደቆጥ ሊያገለግሉ የሚችሉ ርብራቦችን በመጠቀም፤ ከጎረቤቶችዎ ጋር በመቧደን፤ እውቀት በመካፈል፤ የስራ ቁሳቁሶችን በመዋዋስ መጀመር እንደሚቻልም ተመልክቷል።

በሂደቱ ጠንካራ ጉርብትና እና ማኅበረሰብ እንደሚፈጠርና ትኩስ ምርት ከጓሮዎ ማግኘት እንደሚቻልም ተጠቁሟል ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review