የከተማ ግብርና የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ከማጎልበቱ ባሻገር የከተማ ምጣኔ ሃብትን እና የሥራ ፈጠራን ያሳድጋል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing የከተማ ግብርና የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ከማጎልበቱ ባሻገር የከተማ ምጣኔ ሃብትን እና የሥራ ፈጠራን ያሳድጋል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN-መስከረም 20/2017 ዓ.ም

የከተማ ግብርና የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ከማጎልበቱ ባሻገር የከተማ ምጣኔ ሃብትን እና የሥራ ፈጠራን ያሳድጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “የከተማ ግብርናን ሥራ የከተማ የአኗኗር ዘይቤ ስትራቴጂ አካል አድርገን ስናስፋፋ የማሻገር አቅሙ ላይ ጥርት ያለ መረዳት ይዘን ነበር” ብለዋል።

የከተማ ግብርና የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ከማጎልበቱ ባሻገር የከተማ ምጣኔ ሃብትን እና የሥራ ፈጠራን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።

ሀገር አቀፉን የምግብ ዋስትና ያጎለብታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከተማ ልማት ሥራን ይደግፋል፣ ተጠቃሚዎችን በቀጥታ ከአምራች የአካባቢው ገበሬዎች ጋር ያገናኛል ብለዋል።

“ያለንን ውስን ቦታ እንደ የግድግዳ ላይ እና የደረጃ ግብርናን ብሎም ቁሶችን በድጋሚ በሚገባ በመጠቀም ምርታማነትን በማሳደግ የአካባቢ ተጽዕኖን መቀነስ ችለናል” ነው ያሉት።

በመላው ሀገሪቱ የከተማ ግብርና የከተሞችን ሁኔታ በመተለም እና ኢኮኖሚያችንን በማጠናከር ያለውን ጉልበት በማሳየት ከአሁኑ አመርቂ ውጤቶችን በማስገኘት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ ሁሉ ጥረቶቻቸውን የበለጠ እንዲያጠናክሩ ሌሎችም በዚህ በማደግ ላይ ባለ እና የከተሞችን ዘላቂ ነገ በሚያረጋግጥ ተግባር እንዲሳተፉና እንዲያበረታቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review