የከፍታ መንገድ፡- አገልጋይነት

You are currently viewing የከፍታ መንገድ፡- አገልጋይነት

የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ህግ በመተላለፉ ምክንያት ከፈጣሪው ጋር ተለያይቶ ይኖር ነበር፡፡ በጥፋቱ ተፀፅቶ ይቅርታ ካቀረበ በኋላ፤ እግዚአብሔር      “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ከ5 ሺህ 500 ዘመን በኋላ አድንሃለሁ” የሚል ቃል ኪዳን ሰጥቶት ነበር፡፡ በአበው ሲታሰብ የነበረው ተስፋ፣ በነቢያት ሲነገር የነበረው ትንቢት፤ ሲቆጠር የነበረው ሱባኤ ሲፈፀምም ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተፀንሶ ከነፍሷ ነፍስ፣ ከስጋዋ ስጋ ነስቶ በቤተልሔም በከብቶች  በረት እንደተወለደ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ዜና ቀድሞ ያበሰረ አልነበረም። እረኞች ነቅተው ከብቶቻቸውን ከአራዊት፣ ከነጣቂና ሌባ ይጠብቁ ስለነበር ቀድመው    ሰምተዋል። ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሀዲስ የእረኞች ትጋትና ንቃት ለ5 ሺህ 500 ኪዳን ትርጓሜ መምህር ለይኩን ዘመን ሲጠበቅ የነበረውን ትንቢት ብርሃኑ ይናገራሉ፡፡ መገለጡን እንደሚያሳይ መምህር ድንግል ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስን ለይኩን ያስረዳሉ፡፡ ስትወልድ     ከሰማይ      ሰራዊትና ከእረኞች     በስተቀር     የመወለዱን መምህር ለይኩን አክለው እንደገለጹት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ እንኳን ሊኖርበት በማይችልበት ቦታ በከብቶች በረት መወለዱ ፍፁም ትህትናውን ያሳያል፡፡      ከእግዚአብሔርነት    በላይ ልዕልና እና ክብር የለም፡፡ ሱራፌልና ኪሩቤል      እየፈሩ፤      እየተንቀጠቀጡ የሚያመሰግኑት አምላክ በመጀመሪያ ሰውን መስሎ መወለዱ፤ ከሰውም በላይ እንስሳት በሚያድሩበት መወለዱ ፍፁም ትህትናውን ያሳያል፡፡ ይህም ክብሩን አይቀንስበትም፤ ምክንያቱም በከብቶች በረት አካባቢ መላእክት “እነሆ ክርስቶስ ተወልዷል” እያሉ አመስግነዋል፤ አብስረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የወጣቶች ሀዋርያዊ አገልግሎት አስተባባሪ እና በመድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ቁምስና አገልጋይ ካህን አባ መልካም ንጉሴ

በኢትዮጵያ   ካቶሊካዊት    ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የወጣቶች ሀዋርያዊ አገልግሎት አስተባባሪ እና በመድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ቁምስና አገልጋይ ካህን አባ መልካም ንጉሴ በበኩላቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ እያለ በከብቶች በረት መወለዱ የአምላክ ልዕልናው ትህትናው፤ የመለኮት ጉልበቱ በቀል ሳይሆን ምህረት መሆኑን ያሳያል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ትልቅነቱን የገለጠው ትህትና በተሞላበት ፍቅር ነው፡፡ “ራስን ማስቀደም”፣ “ራስን ማሳየት” እንደ ትልቅነትና ኃያልነት በሚወሰድበት በዚህ ዓለም የአምላክን አካሄድ መረዳት ሊያስቸግር ይችላል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኃያልነት ግን ፍቅርን በማስቀደምና ራስን በመስጠት የሚገለጥ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት ሲወለድ እንስሳቱም ትህትናን አሳይተዋል፡፡ ከሰው ጋር ያላቸው መስተጋብር፣ ሰዎችን የማገልገል፣ ሰዎችን የመልመድ ማንነታቸውጌታ በመሀላቸው ቆሞ በመገኘቱ ታይቷል፡፡ ይህም ትህትናቸውን እንደሚያሳይ ያስረዳሉ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ     “ቤተልሔም” በተባለች ከተማ በከብቶች በረት ነው የተወለደው፡፡ ቤተልሔም የድሆች ከተማ ናት፡፡ ሰማሪያ፣ ኢያሪኮ፣ እየሩሳሌም እንደሚባሉት የእስራኤል ከተሞች ትልቅ አልነበረችም፡፡ መንደር ነበረች፡፡ ነገስታት ሲሾሙ የሚታወቁት ትላልቅ ከተማ ላይ ከሆነ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን በተናቀ ቦታ ላይ ትልቅ ቁም ነገር ማድረግን እንደሚችል፣ የትልቅነት መለኪያው ትህትና እንደሆነ ለማሳየት በቤተልሔም እንደተወለደ አባ መልካም ያነሳሉ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት ብዙ የትህትና ስራ በትምህርት እንዳስተማራቸው፤ በተግባር ሰርቶ ሲያሳያቸው እንደነበር መምህር ለይኩንም ያነሳሉ፡፡ እነሱ ግን የትኛው ስራ ነው ትልቁ ወይም የሚበልጠው? እያሉ ይጠይቁት ነበር፡፡ እሱ ይህ ዓለም የሥራ እንደሆነ፣ ሰው የሚከብረው በትህትና ሰርቶ፣ ራሱን ዝቅ አድርጎ እንጂ ከፍ በማድረግ የሚከበር እንደሌለ፣ በፍቅር የኖረ ክብርና የመጨረሻውንመክሊት የሚያገኝ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ “እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ፡፡ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ይገባችኋል” ሲል በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13፡13-14 ያለውን ሀይለ ቃል በማንሳት ያስረዳሉ፡፡

ትህትና ከዝቅታ የሚገኝ ወደ ከፍታ የሚወሰድ መንገድ በመሆኑ በዕለት ተዕለት ህይወታችን ልንላበሰው ይገባል። አባ መልካም እንደሚያስረዱት፣ የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲኖር የተጠራበት ዓላማ ለአንድና አንድ ነው፤ እሱም የፍቅር ጥሪ፡፡ አንድም ፈጣሪውን እንዲያፈቅር፣ ሁለትም ከመሰሎቹና    ባልንጀሮቹ ጋር በሰላምና በስምምነት እንዲኖር ይጠበቃል፡፡

አገልጋይነትን እንዴት እንላበስ?

የኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት መወለድ የሚያስተምረው ብዙ ቁም ነገር እንዳለ መምህር ለይኩን ያስረዳሉ። በየትኛውም መስክ የተሰማራ ሰው፣ የተሰጠው ኃላፊነት ከእግዚአብሔር እንደሆነ መረዳት አለበት፡፡ ስልጣን፣ ገዥነት፣ እውቀት፣ የሀብት ባለቤት እግዚአብሔር ነው ብሎ ራስን ማሳመን ያስፈልጋል፡፡ ሰው ከሌላው ያላገኘው፣ ያልተዋሰው፣ ያልኮረጀው ምንድን ነው? “ከእግዚአብሔር ያልተሰጠህ ምንድን ነው?” እንዲል መጽሐፉ፡፡

እያንዳንዱ ሰው ከአካል ጀምሮ እስከ ማሰብ፣ ማሰላሰል፣ ያለፈውን ማስታወስ፣ ዛሬ ያለውን፣ ወደፊት የሚሆነውን መናገር የሚያስችለው ትልቁ አእምሮ ድረስ ተሰጥቶታል፡፡ ሀብት፣ እውቀት፣ ስልጣንም ሆነ ውበት የእግዚአብሔር ነው ብሎ የሚያምን ሰው ክፉ ነገር ከመስራት መቆጠብ እንዳለበት መምህር ለይኩን ይመክራሉ፡፡

“ለራስህ(ሽ) እንዲደረግ የምትፈልገውን መልካም ነገር ለሌላው አድርግ” የሚል በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ወርቃማ ህግ አለ፡፡ በትህትና የሰጠነው ፍቅር መልሶ ይከፍለናል፡፡ በመንግስትና በተለያዩ የሲቪል አስተዳደሮች በትህትና ማገልገል ሀገር የበለጠ ይገነባል፤ መልካም ስብእናንም ያሳድጋል፡፡

አባ  መልካም እንደሚያስረዱት፣ ዛሬ በተለያየ መልኩ የሚታዩ ችግሮች “ከእኔነት” እና ትዕቢት የሚመነጩ ናቸው፡፡ ለዚህም መድሃኒቱ ትህትና ነው፡፡ ትህትና የማያሸንፈው ፍጡር የለውም። የሰው ልጅ አስፈሪ አውሬዎችን ሲያላምድና ሲገራ ይታያል። ሰው ደግሞ ከአራዊት የበለጠ ስብዕና የተላበሰ ትልቅ ፍጡር ስለሆነ በትህትና ውስጥ በመመላለስ ዓለምን ማቅናት እንዳለበት ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል። የክርስቲያን የህይወት ጥሪና ዓላማም በትህትና በመመላለስ በየተሰማራበት መስክ መገለጥ ይኖርበታል፡፡

መምህር ለይኩን በበኩላቸው፣ ሰው ሁሉ ነገር ከፈጣሪው በልግስና የተሰጠው ይዞ ለሌላው መትረፍ፤ ጊዜውን ሳይጠቀምበት ሞት እንዳይቀድመው መስራት እንዳለበት ይናገራሉ፡፡ በስልጣን፣ በሀብት፣ በተለያየ ስጋዊም ሆነ መንፈሳዊ የከፍታ ደረጃ የሚገኙ ሰዎች የተሰጣቸው ኃላፊነት ከእግዚአብሔር ነው ብለው ዝቅ ብለው ማገልገል አለባቸው፡፡ ተገልጋይ ላይ ፊታቸውን ቢያጠቁሩ፣ ግፍ ቢፈፅሙ፣ ፍርድ ቢያጎድሉ፣ ተገልጋዮች የሚያነቡት ወደ አገልጋዩ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ሲፈርድ ደግሞ የቃል ወይም የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ አይሰጥም፤ ልክ እንደሞት ሳይታወቅ የሚደርስ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ማንኛውም ሰው በትህትና ዝቅ ብሎ ካልሰራና አርዓያነቱን ካላሳየ የትም መድረስ አይችልም፡፡ ይህ ዓለም የስራ በመሆኑ የምንሰራውም ስራ በፍቅር የተሞላ መሆን አለበት፡፡ ትጉሁ ሰው በመጨረሻው ጊዜ ሲጠየቅ “አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ፤ በአምስቱ ላይ አምስት ጨምሬበታለሁ” ብሎ ያበረክታል፡፡ ሰነፍ አገልጋይ ከሆነ “መክሊትህን ለምንድን ነው ወደ ቦታው ያልመለስክ?” የሚል አምላካዊ ተግሳፅና ጥያቄ ይጠብቀዋል፡፡ ከምንም በላይ በቅንነት ማገልገል ራሳችን፣ ቤተሰባችን፣ ማህበረሰባችን ብሎም ሀገራችንን የሚገነባ መሆኑን አውቀን መስራት እንደሚገባን መምህር ለይኩን ያስገነዝባሉ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት መወለድ ፍቅርን፣ ትህትናን፣ መተሳሰብን ማስቀደም እንዳለብን እንደሚያስተምር ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን ያጋሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪው አቶ ሞሲሳ ኦሊቃ ናቸው፡፡ አቶ ሞሲሳ፣ “በየትኛውም የኃላፊነት ደረጃ ያለ ሰው፤ ሁሉንም ሰው በትህትና ማስተናገድ እና በእኩል ዓይን ማየት ይኖርበታል።

እኔ የህክምና ባለሙያ ነኝ፤ የህክምና ባለሙያ እንደመሆኔ ሰዎችን በአለባበስ፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በሀብት ደረጃ ወዘተ ልዩነት በማድረግ ማስተናገድ የለብኝም፡፡ እንደ ጤና ባለሙያ ስመረቅ፤ ነጭ ልብስ ስለብስ ማንኛውንም ሰው ፈጣሪ በሰጠኝ እውቀትና ጥበብ እኩል ለማገልገል ቃል ገብቼ ነው” ይላሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ትህትናን ተላብሰው የሚያገለግሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ቅንነት በማጣት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የማይወጡ እንዳሉ አስተያየት ሰጪያችን ያነሳሉ፡፡ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የምንማረው ግን ከሁሉም በላይ ዝቅ ብለንና ሰውነትን በማስቀደም ማገልገል እንዳለብን ነው፡፡ ሰውነትን ማስቀደም ከቻልን የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደምንችል ገልጸዋል፡፡

የገናን በዓል ስናከብር የኢየሱስ ክርስቶስን የትህትና ስራ እያሰብን ሁላችንም በየተሰማራንበት መስክ ምን ያህል በትህትና እያገለገልን ነው? ብለን ራሳችንን መለስ ብለን በማየት መሆን ይኖርበታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ልደቱን ስናከብር ምንድን ነው የማስተካክለው? በሚል ራስን መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ ዝቅ ብሎ ቤተሰብን፣ ሰፈርን ማገልገል በሀገር ደረጃም የተሻለ ለውጥ ለማምጣት እንደሚቻል አቶ ሞሲሳ ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑት አቶ ሽመልስ ቢራቱ ናቸው፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ በበረት መወለድ እኛም ዝቅ ብለን በትህትና እንድናገለግል የሚያመላክት ነው፡፡ በተሰማራንበት ሙያ በአክብሮት አገልግሎት ልንሰጥ ይገባል፡፡

አሁን ላይ በህዝብ እና የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገልጋይነት ክፍተት ይታያል፡፡ አገልግሎትን ከጥቅም ጋር አያይዞ የመስጠት ጉዳይም ይስተዋላል፡፡ ሰው ወደ አንድ መስሪያ ቤት ሲሄድ “ምን ያህል ገንዘብ እጠየቅ ይሆን?” እያለ እየፈራ ነው የሚሄደው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ዝቅ ብሎ ሌላውን ሲያገለግል ነው የታየው የማያዩትን አይን ሲያበራ፤ ህሙማንን ሲፈውስ፣ ሙታንን ሲያስነሳ ለአንድም አገልግሎቱ ገንዘብ አልጠየቀም፤ እውቅናም አልፈለገም። እኛም ይህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በትህትና ማገልገል ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው አስተያየት ሰጪያችን የከተማዋ ነዋሪ መምህር አስማረ አንላይ በበኩላቸው፣ የኢየሱስክርስቶስ በከብቶች በረት መወለድ ከዝቅታ ከፍታ እንደሚገኝ ያስተምራል፡፡ ራስን ዝቅ ማድረግ ከፍታን ያመጣል፡፡ ክርስቶስ እንዳስተማረው በእውነት ትህትናን ተላብሰን እያገለገልን ነው ወይ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ አጠያያቂ ነው፡፡ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የሚወጡ፣ መልካም ስነ ምግባር ተላብሰው፣ ጎንበስ ቀና ብለው የሚያገለግሉ እንዳሉ ሁሉ፤ አገልጋይነት የሚጎድላቸው ይታያሉ፡፡ በአንዳንድ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የቢሮ ኃላፊ ወይም ባለሙያው በስራ ሰዓት ቢሮ ባለመገኘት ተገልጋይን ማጉላላት፣ ቢሮ ቢቀመጡ እንኳን ለተገልጋይ ጥሩ ፊት የማያሳዩ፣ ችግርን ለመፍታት ዝግጁ ያልሆኑ፣ ተገልጋዩ ተለማምጦ፣ የእጅ መንሻ አቅርቦ ጉዳዩ እንዲፈፀምለት የሚፈልጉ አሉ፡፡ በማባበል፣ የአገልግሎት ጠያቂውን የሀብት ደረጃ ወይም ሌላ በማየት የሚያስተናግዱም እንዳሉ መታዘባቸውን ያነሳሉ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ያለውን ትርጉም በትክክል ተረድተን ህይወታችንን ልንመራበት ይገባል፡፡ በዝቅታ ውስጥ ከፍታ፤ በማክበር ውስጥ መከበር መኖሩን በመረዳዳት፣ በመተጋገዝ ሀገርን የበለጠ ለማገልገል በመዘጋጀት ሊሆን እንደሚገባ በከብቶች በረት መወለድ በየተሰማራንበት መስክ ትህትናን ተላብሰን አገልግሎት መረዳት ይኖርብናል፡፡ የገና በዓልን ስናከብር ሁላችንም በየተሰማራንበት መስክ ዝቅ ብለን በማገልገል፣ እርስ በርስ በመረዳዳት፣ በመተጋገዝ ሀገርን የበለጠ ለማገልገል በመዘጋጀት ሊሆን እንደሚገባ መምህር አስማረ ያነሳሉ፡፡

የሃይማኖት አባቶችም ሆነ ምዕመናን እንደተናገሩት   የኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት መወለድ በየተሰማራንበት መስክ ትህትናን ተላብሰን አገልግሎት መስጠት እንዳለብን፣ ይህንን የህይወታችን አካል ብናደርገው ብዙ ማትረፍና ማግኘት እንደምንችል ያሳያል፡፡

በስንታየሁ ምትኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review