የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከልን እየጎበኙ ነው

You are currently viewing የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከልን እየጎበኙ ነው

AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከልን እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡

ማዕከሉ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየጎበኙት ይገኛሉ።

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በጉብኝታቸው ወቅት ፣ አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ሁሉንም በአንድ ቦታ የያዘና የኢትዮጵያን ብሎም የአዲስ አበባን ጀምሮ የመጨረስ አቅም ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል በርካታ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በአንድ ቦታና በቀላሉ ሁሉንም አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ 40ሺ ሄክታር ላይ ያረፈ አለም አቀፍ ማዕከል ነው።

ሬስቶራንቶች፣ በርካታ የንግድ ሱቆች፣ ባንኮች እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያካተተ በሀገራችን ትልቁ የኮንፍራንስ ማዕከል ነው።

በከተማችን ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ አደባባይ ከሆነው ከሆነው የለሚ ፓርክ ጋር ተያይዞ የተሰራ ዓዕከል ነው።

አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል እስከ ቀጣይ እሁድ ማለትም እስከ የካቲት 30 2017 ዓ.ም ድረስ ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆንም ተገልጿል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review