AMN-ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት የጎላ ሚና የሚኖረው የካፒታል ገበያ በአንጋፋው የኢትዮ ቴሌኮም የ10 በመቶ የአክስዮን ሽያጭ ስራው ተጀምሯል፡፡
ይህንን አስመልክተው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣
የካፒታል ገበያ በሀገራችን ኢንቨስትመንትና ቁጠባን ከማሳደጉ ባሻገር አካታች የፋይናንስ ዘርፍን በማሳደጉ ረገድ ትልቅ ሚናን ይጫወታል ብለዋል፡፡
የ130 አመታት ዕድሜ ባለፀጋው ኢትዮ ቴሌኮም፤ 10 በመቶ የአክስዮን ድርሻውን በሽያጭ ለሕዝብ ማቅረቡ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የካፒታል ገበያው ጅማሬ ኢትዮጵያን ወደ ተሳለጠ እና ዘመናዊ የአክስዮን ገበያ ስርዓት የሚያስገባትና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ ድንቅ ክዋኔ መሆኑንም አንስተዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን ብለዋል።