AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
የኮሪደር ልማት ስኬታማነት በሀገር ወዳድ ዜጎች ትብብር እና በተቋማት ቅንጅት የተመዘገበ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ፡፡
ከሳዉዝጌት ዲያስፖራ አደባባይ መገናኛ እስጢፋኖስ መስመር በሁለተኛዉ ዙር የኮሪደር ልማት በስራ ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት የእራት ግብዣ አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ለኮሪደር ልማት በስኬት መታጀብ ግለሰቦች እና ተቋማት ከሀሳብ ጀምሮ የሚለግሱት ድጋፍ ትልቅ ሚና ስለመጫወቱ ተናግረዋል፡፡
ይህ ትብብር እና ቅንጅት በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበዉ ሚደቅሳ፣ ለከተማዋ ሁለንተናዊ ልማት ባለስልጣኑ የራሱን ሚና መወጣቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ሁለተኛዉ ዙር የኮሪደር ልማት በ24/7 የስራ ባህል በህዝብ እና በመንግስት ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በተመስገን ይመር