የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርኪዬ በሆቴል ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ለደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ
AMN – ጥር 13/2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርኪዬ ቦሉ ግዛት በአንድ ሪዞርት ሆቴል ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ በደረሰው የሰዎች ህልፈት እና የአካል ጉዳት ሀዘኑን ገልጿል፡፡
ለሟች ቤተሰቦች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የገለጸው ሚኒስቴሩ በደረሰው አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ፈጣን ማገገምን ተመኝቷል፡፡
የኢፌዴሪ መንግስት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከቱርክ መንግስትና ህዝብ ጎን እንደሚቆም ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል፡፡
በቱርኪዬ በአንድ ሪዞርት ሆቴል ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ በትንሹ የ66 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡