የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ ካሊፎርንያ ግዛት በተከሰተ ሠደድ እሳት በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ

You are currently viewing የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ ካሊፎርንያ ግዛት በተከሰተ ሠደድ እሳት በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ

AMN – ጥር 2/2017 ዓ.ም

የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ የካሊፎርንያ ግዛት ሎስአንጀለስ አካባቢ በተከሰተ ሠደድ እሳት በደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በአሜሪካ ሎስአንጀለስ አካባቢ የተከሰተውን ሠደድ እሳት ተከትሎ በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋት፣ መፈናቀል እንዲሁም የሀብት ንብረት ውድመት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ ሕዝብና መንግስት፣ ጉዳት ካስተናገዱ አሜሪካዊያን እና መሰረታቸው ከኢትዮጵያ ከሆኑ የሎስአንጀለስ ነዋሪዎች ጎን እንደሆነ አጋርነቱን በመግለጫው አረጋግጧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review