AMN – ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም
17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት ተከብሯል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ለአገር ሉዐላዊነት እና አንድነት የተከፈለ መስዕዋትነት በማስታወስ ሊሆን ይገባል ብለዋል ።
በዚህ ቀን በዓመቱ በመንግሥት የታቀዱ የልማት ተግባራትን ለማሳካት በሰንደቅ ዓላማችን ፊት ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል።
ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችን እና የፖን አፍሪካ ንቅናቄ ምልክት እና መነሻ በመሆኑ ትልቅ ዕሴት መሆኑን መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
የዘንድሮው 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ”ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ በመላው አገሪቱ እና በመላው ዓለም በሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤቶች እየተከበረ ነው።