AMN-የካቲት 8/2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ለተመረጡት ለጅቡቲው ማህሙድ አሊ የሱፍ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፏል፡፡
እንዲሁም ከአልጀሪያ በምክትል ኮሚሽነርነት ለተመረጡት አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ የእንኳን ደስ አልዎ መልዕክት አስተላልፏል።
ሚኒስቴሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት፣ አዲስ በተመረጡት የህብረቱ አመራሮች የስራ ዘመን የአህጉሪቱ የልማት አጀንዳዎች መተግበራቸው እንደሚቀጥል ያለውን እምነት ገልጿል።