የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ

You are currently viewing የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ

AMN- መስከረም 23/2017 ዓ.ም

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታወቀ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት መደገፍ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት ለመሆን እሰከ አሁን ያለፈቻቸውን ሂደቶች እና የወሰደቻቸውን እርምጃዎች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መንግስት ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል እንድትሆን ቁርጠኛ እና ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ አባል የመሆን ጥረት የተሳለጠ እንዲሆን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እየወሰደች ያለችውን እርምጃና የሄደችበትን ርቀት አድንቀዋል።

ባንኩ ኢትዮጵያ እያደረገች የምትገኝውን ጥረት በፋይናንስና በቴክኒክ እንደሚደግፍ ኃላፊዎቹ መግለጻቸውን ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review