AMN- ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም
የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ተቋም ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት የሚያደርጉትን ድጋፍ ኢትዮጵያ እንደምታደንቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ባለው የጂ 24 የገንዘብ ሚኒስትሮችና የባንክ ገዥዎች ስብሰባ እየተሳተፈች ነው ፡፡
በገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ የተመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልዑኩ ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የምታራምደውን አቋም አብራርተዋል።
ሀገራት ከወለድ ጫና ተላቀው ተመጣጣኝ በሆነ ወለድ ገንዘብ ማግኘት እንዳለባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል ።
በዚህ ረገድ የዓለም ባንክ እና አይ ኤምኤፍ ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡