AMN- የካቲት 20/2017 ዓ.ም
የዓድዋ ድል በአንድነት የመጣ ድል በመሆኑ የአሁኑ ትውልድም ድሉን ስንቅና እርሾ በማድረግ ከፋፋይ አስተሳሰቦች፣ ግለሰቦች እና ቡድኖችን ወደ ጎን በመተው ብሔራዊነትን በማጉላት ለሀገር እድገት መስራት ይገባዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ጥሪ አቅርበዋል።
በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች “አድዋ የጥቁር ህዝቦች ቀን” በሚል መሪ ሀሳብ 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ መርሐ-ግበሮች እየተከበረ ይገኛል::

በአራዳ ክፍለ ከተማ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ ድሉ ከጦርነት ድል በላይ የአፍሪካውያን የአንድነት እና የጥንካሬ መገለጫም ጭምር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የዓድዋ ድል በአንድነት የመጣ ድል በመሆኑ የአሁኑ ትውልድም ድሉን ስንቅና እርሾ በማድረግ ከፋፋይ አስተሳሰቦች ግለሰቦችና ቡድኖችን ወደ ጎን በመተው ብሔራዊነትን ማጉላት እና ለሀገር እድገት መስራት ይገባዋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል::
በበዓሉ ላይ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የክፍለ ከተማው አመራሮች እና ነዋሪዎች ታድመዋል፡፡
በአንዋር አህመድ