የዘንድሮውን የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕብረብሔራዊ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

You are currently viewing የዘንድሮውን የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕብረብሔራዊ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

AMN – ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም

19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕብረብሔራዊ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሰራ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገዛኸኝ ጋሞ ገለፁ።

19ኛው የኢትዮጵያ የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለሕብረብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባምንጭ ከተማ ሕዳር 29 ቀን 2017 ይከበራል።

በዓሉ የኢትዮጵያውያን ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶቻቸው የሚንጸባርቁበት፤ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነታቸውን ለመላው ዓለም የሚያሳዩበትም እንደሆነ ይታወቃል።

የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ገዛኸኝ ጋሞ እንደገለጹት፤ የብሔር ብሔረሰብ ቀን የኢትዮጵያ ብዝሃ ማንነት የሚንፀባረቅበት ነው ብለዋል።

በዓሉ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት፣ አንድነት፣ ፍቅርና ብዝሃነት የሚረጋገጥበት በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

በዓሉ የሀገርን ብሎም የክልሉን ገፅታ የሚገነባ በመሆኑ ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ከተማ አስተዳደር ድረስ በከፍተኛ አመራር የሚመራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ዕቅድ በማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዝግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review