የዘንድሮ የአረንጓዴ ዓሻራ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥርዬን አቀርባለሁ:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing የዘንድሮ የአረንጓዴ ዓሻራ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥርዬን አቀርባለሁ:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- ሀምሌ 12/2016 ዓ.ም

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዓሻራ መርሀ-ግብር ላይ ሁሉም ተካፋይ እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር በመሆን በጫካ ፕሮጀክት ሀገር በቀል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተክለዋል።

የባህር ዛፍን በሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች የመተካቱ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር “የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ላይ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review