የዚህ ትውልድ አሻራ በትክክል እየተቀመጠ ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የዚህ ትውልድ አሻራ በትክክል እየተቀመጠ ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም

የዚህ ትውልድ አሻራ በትክክል እየተቀመጠ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በአይሲቲ ፓርክ በመገኘት የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

ከንቲባ አዳነች የአረንጓዴ አሻራቸውን ባኖሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ በዛሬው ዕለት እየተከናወነ ባለው የችግኝ ተከላ የከተማዋ ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ እየተከለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በከተማዋ 168 አካባቢዎች ተካላው እየተካሄደ እንደሚገኝ የገለጹት ከንቲባዋ፣ በ250 ሄክታር መሬት ላይ 6 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ ገልጸዋል።

የዛሬው ችግኝ ተከላ መርሀግብር አስደማሚ መሆኑን አውስተው፣ በዚህም የደን ሽፋኑ እንደሚጨምር ተናግረዋል።

የአረንጓዴ አሻራው መጨመር ለወደፊቱ የአገሪቱ እድገትና ብልጽግና ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ አንስተዋል።

የችግን ተከላው መርሀግብር ለአየር መዛባቱ መፍትሄ እንደሚሆንም ነው የጠቀሱት።

የአረንጓዴ አሻራን ማስቀመጥ ለዛሬው ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለነገውም ጭምር ትልቅ ትሩፋት ነው ሲሉም አክለዋል።

በመሆኑም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከለው ነዋሪ ትልቅ ትንሽ ሳይሉ በነቂስ ወጥተው እየተከሉ እንደሚገኙ የተናገሩት ከንቲባ አዳነች፣ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን በእንክብካቤው ሂደትም ተገቢው ስራ ሊሰራ ይገባዋል ብለዋል።

እስከ ዛሬ ከተተከሉ ችግኞች በአዲስ አበባ ላይ ከ86 በመቶ በላይ መጽደቃቸውን ገልጸው፣ ሀገር የምትለወጠው በጋራ ጥረትና ትብብር ነው ብለዋል።

“የዚህ ትውልድ አሻራ በትክክል እየተቀመጠ ነው፤ በዛሬ ውሎ እንደ ሀገር 600 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ ያወሱት ከንቲባ አዳነች የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ከዚህም በላይ ከሆነ ሙሉ ቀን በርካታ ችግኞች ሊተከሉ እንደሚችሉ አንስተዋል።

በሰለሞን በቀለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review