AMN- ህዳር 5/2017 ዓ.ም
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግስት አቅንተው ከረዥም ጊዜ ተቀናቃኛቸው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ተነጋግረዋል፡፡
የዛሬ አራት አመት ትራምፕ ተሸንፈው ከዚሁ ቢሮ በወጡበት ወቅት ለባይደን ያላደረጉትን አይነት አቀባበል ነው ባይደን ለትራም ያደረጉላቸው፡፡
ትራምፕ በምርጫው ድል ስለቀናቸው “እንኳን ደስ አለህ ” ያሉት ባይደን፤ “ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግርም ይኖረናል” ብለዋል፡፡
ትራምፕ በበኩላቸው ባይደንን አመስግነዋል፡፡
አቀባበሉን አስመልክቶ ይህ የቆየ የአሜሪካ የዲሞክራሲ ባህል ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የአሜሪካንን ህዝብ የሚመጥን ተግባር በመሆኑ መደረግ ያለበት ትክክለኛ ነገር ነው ሲሉ የነጩ ቤተ መንግሥት ፀሀፊ ካሪኔ ጄን ፔር ገልጸዋል ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡