የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የመጪውን ፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 216 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል።
በክልሉ ባሉ ማረሚያ ቤቶች በህግ ፍርድ አግኝተው ሲታረሙና ሲታነጹ ከቆዩ ታራሚዎች መካከል የይቅርታ ጥያቄ ካቀረቡት ወስጥ በይቅርታ አዋጅ፤ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ ታራሚዎችን መሆኑም ተገልጿል።
የይቅርታ ቦርዱ ከመንግስት ፤ከህዝብና ከታራሚ ጥቅም አንፃር በጥልቀት መርምሮ ወንድ 1 ሺህ 183 ሴት 33 ድምር 1 ሺህ 216 ታራሚዎች የይቅርታ ተጠቃሚ መደረጋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
All reactions:
11