የጀርመን የፓርላማ አባላት የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት ለማሻሻል እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ

  • Post category:ጤና

AMN – ኅዳር 12/2017 ዓ.ም

የጀርመን የፓርላማ አባላት የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ስርዓት ተሞክሮ ለመመልከትና ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ ድጋፎችን አስመልክቶ ከጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክረተር ደረጀ ዱጉማ ጋር ምክክር አድርገዋል።

በምክክሩም (ዲ ኤስ ደብሊው) የተሰኘ የጀርመን ሀገር ግብረ-ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ላለፉት ሀያ ዓመታት የሰራቸው ስራዎች ምን ያህል ውጤታማ ነው የሚለውን በጋራ ገምግመዋል፡፡

በዋናነትም የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤና ላይ የተከናወኑ ተግባራት ላይ እና በቀጣይም በግብረ ሰናይ ድርጅቱ በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶችና የሚደረጉ ድጋፎች ላይ ትኩረት መደረጉን ዶክተር ደረጀ አስታውቀዋል።

ድርጅቱ በቢሾፍቱ ከተማ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤናማ አኗኗር ላይ አቅም ማጎልበቻ ማሰልጠኛ ማዕከል ከፍቶ እየሰራ ያለና እና የህክምና መስጫ ክሊኒክ እንዳለው የጠቀሱት ዶ/ር ደረጀ፤ እነዚህም የአገልግሎት ማዕከላት ለወጣቶችና አፍላ ወጣቶች በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናዎችንና የስነ ተዋልዶና ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጡ አክለዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ የወጣቶች ህክምና መስጫ ተቋማትንና በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሰሩ ወጣቶችንም ጤና ሁኔታ እንዲሁም ለወጣቶች የስነ ተዋልዶ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ግብዓት አቅርቦትን በአካል ተገኝተው መጎብኘታቸውን ተናግረዋል።

(ዲ ኤስ ደብሊው) በኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣቶችና አፍላ ወጣቶችን የስነተዋልዶ ጤና ላይ ንቃተ ጤናቸውን በማሳደግ፣ ተላላፊ በሆኑ በሽታዎች በተለይም ከኤችአይቪ ራሳቸውን እንዲከላከሉ በማድረግ፣ አስፈላጊ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ግብዓቶችን በማሟላትና በአቅራቢያቸው ከሚገኙ ጤና ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ውጤታማ ስራ እየስራ መሆንኑም ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል።

የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና ይህንንም ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የፓርላማ አባላቱ መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠርና አጠቃላይ የጤና ስርዓቱን ለማሻሻል በሚደረጉ ስራዎች ላይ የፋናንስ ድጋፍም እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review