የገንዘብ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የታክስ ህጎች የመተርጎምና የማደራጀት ስራውን አጠናቆ በድረ-ገጹ ተደራሽ አደረገ

You are currently viewing የገንዘብ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የታክስ ህጎች የመተርጎምና የማደራጀት ስራውን አጠናቆ በድረ-ገጹ ተደራሽ አደረገ

AMN – ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም

ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያን የታክስ ህጎች ለመተርጎምና ለማደራጀት ሌክሲስ ኔክሲስ የህግ የበላይነት ተቋም ከተባለ ድርጅት ጋር ሲያከናውነው የነበረውን ፕሮጀክት በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሚኒሰቴሩ የመስብሰቢያ አዳራሽ አስመርቋል።

ተበታትነው የሚገኙ የተለያየ የታክስ ሀጎችን ባለፉት ሶስት ዓመታት በማሰባሰብ እና በማደራጀት ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የመተርጎም ስራ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

በዚህም መሰረት ሁሉንም የታክስ ህጎችን በማሰባሰብና ለተጠቃሚው ምቹ በሆነ መንገድ በማዘጋጀት በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በገቢዎች ሚኒስቴርና በጉምሩክ ኮሚሽን ድረ-ገጾች ላይ የተጫኑ ሲሆንከዚህ ቀደም በአማርኛ ብቻ ተዘጋጅተው የወጡ ከ110 በላይ የታክስና ቀረጥ መመሪያዎች ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉመዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ይህ ፕሮጀክት ሲጀመር ተደራሽነትን፣ ግልጽነት እና ቅልጥፍናን ማሻሻል በሚሉ ሶስት ዋና ዋና ዓላማዎች ላይ ተመስርቶ እንደነበር አብራርተዋል፡፡

የታክስ ህጎቹ በእንግሊዝኛ ተተርጉመውና ተደራጅተው በድረ-ገጽ ለተገልጋዩ ተደራሽ መደረጋቸው ኢትዮጵያ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው መሰረት እድገትና ልማቷን ለማፋጠንና የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ሀገር ለመሆን ለምታደርገው ጥረት ለዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ስለታክስ ህጎቿ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በድረ-ገጽ ተደራሽ መሆኗ ታላቅ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያን ቁልፍ የታክስ ህጎች ለመተርጎም፣ ለማዋሃድ እና ስራ ላይ ለማዋል በገንዘብ ሚኒስቴር እና በ Lexis Nexis Rule of Law ፋውንዴሽን መካከል ስምምነቱ የተፈረመው እ.ኤ.አ ሰኔ 16 ቀን2022 ላይ እንደነበር ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review