AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር እንደከፈተ ገለፁ ፡፡
በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረጉት ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመስግነዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት።
በሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ ቀጥሏልም ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው።