AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በመዲናዋ በቅዳሜ እና እሁድ የገበያ ማዕከላት በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡
ሸማቾችም የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶችን አቅራቢያ ከሚገኙ የቅዳሜ እና እሁድ የገበያ ማእከላት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱ አመላክቷል።
በየክፍለ ከተማው የኑሮ ዉድነትን በማረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኘው የሰንበት ገበያ የተለያዩ ጥራት ያላቸዉ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ቀርበው እንደሚገኙም ነው ቢሮው የጠቆመው።
ይህም ለህብረተሰቡ አማራጭ የገበያ ቦታ በመሆን በስፋት ግብይት እየተከናወነ መሆኑን መመልከት መቻሉን የቢሮው መረጃ ያመለክታል፡፡