የጤና መረጃ

  • Post category:ጤና

AMN – ጥር 6/2017 ዓ.ም

የደም ማነስ መንስኤ፣ ምልከቱ እና መከላከያው/ህክምናው

የደም ማነስ የሚባለው በሰውነታችን ውስጥ በቂ የሆነ የቀይ ደም ሴሎች አለመኖርና ተገቢ የሆነ ስራቸውን ባግባቡ ሳይሰሩ ሲቀር የሚከሰት የደም ሕመም መሆኑን የክሊቭላንድ ክሊኒክ መጀረጃ ያመላክታል፡፡

የደም ማነስ አንዳንዴ በዘር የሚተላለፉ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በሂደት ሊከሰት እንደሚችል ተመላክቷል፡፡

የደም ማነስ ህመም በቶሎው ህክምና በማድረግ ካልተከላከሉት ቀላልና ከባድ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ያስገነዝባሉ፡፡

መንስኤው

የደም ማነስ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእዚህም መካከል ከሚመገቡት ምግብ ውስጥ በቂ ብረት አለመኖር እና ደካም የአመጋገብ መንገድን መከተል በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

ምልክቶቹ

የደም ማነስ በሽታ ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል፡-

ድካም፣

ማዞር፣

የቆዳ መገርጣት፣

የልብ ምት እና የትንፋሽ ማጠር፣

ራስ ምታት፣

ተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖች መከሰት፣

የደረት ሕመም፣

የእንቅልፍ ማጣት፣

ማቅለሽለሽ ወይም የሆድ ህመም፣

መፍዘዝ ወዘተ ይገኙበታል፡፡

ሕክምናው/ መከላከል

በዕለት ተዕለት አመጋገባችን ውስጥ በብረት የበለፀጉ ምግቦችን በመመገብ የብረት እጥረት ማነስን መከላከል ይቻላል።

እንዲሁም ጤናማ የአመጋገብ ዘዴን መከተል፣ ብዙ ውሃ መጠጣት፣ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የእጅን ንጽህና መጠበቅ፣ የቫይረስ እና የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል የሚረዱ ክትባቶችን በመውሰድ የደም ማነስ በሽታን መከላከል የሚቻል ሲሆን ነገር ግን በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን ጨምሮ አንዳንድ የደም ማነስ አይነቶችን በቀላሉ ለመከላከል እንደማይቻል ከክሊቭላንድ ክሊኒክ ያገኘነው የጤና መረጃ ያመላክታል፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review