የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚገኙ ጤና ባለሙያዎች እና ታካሚዎች ጋር የትንሳኤ በዓልን አክብረዋል።
ሚኒስትሯ የጤና ባለሙያዎችን ያበረታቱ ሲሆን ለታካሚዎችም ስጦታ አበርክተዋል።
የጤና ሙያ ራስን ሰጥቶ ህብረተሰቡን ማገልገል ዋንኛ መገለጫው መሆኑንም ገልጸዋል።
ለሕብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ከማሻሻል ጎን ለጎን የጤና ባለሙያውን ሕይወት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀየር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ዶክተር መቅደስ ዳባ ከሌሎች የሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር በመሆን በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ተገኝተው ማዕድ በማጋራት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሚኒስትሯ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዘመናዊ የአልትራሳውንድ ማሽን ድጋፍ አበርክተዋል።